አሳመረልኝ
Asamerelegn
2014 · ትራክ 12 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጓዳዬ ሆኜ የልቤን
ነገርኩት የውስጥ የሆዴን
በጊዜው ጌታ መጣና
አሳመረልኝ ድንቅ አረገና (፪x)
አዝማች · Chorus
አሳመረለኝ አሃሃ ድንቅ አረገና (፪x)
አሳመረልኝ አዎ ድንቅ አረገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ እኮ ነው የራራልኝ የራራልኝ
ያንን ዘመን ያሻገረኝ ያሻገረኝ
ዘምራለሁ ለዚህ ጌታ
ያረገልኝ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
ይዤ ልግባ ማደሪያው
ምሥጋናዬ ያውድ መዓዛው
አዝማች · Chorus
ያውድ መዐዛው ይብዛ ዕልልታው (፪x)
በማደሪያው ምሥጋናው
በማደሪያው ዕልልታው
በመቅደሱ ምሥጋናው
በመቅደሱ ዕልልታው
ቁጥር 3 · Verse 3
አላስኬድ ያሉኝ ከፊቴ ቆመው
ህልሜን ተስፋዬን ሁሉ አጨልመው
መንገዴን ዘግተው በቆሙት ላይ
ቁጣው ነደደ መጣ ከላይ
በበቀል እሳት ወረደባቸው
ግድብ እንዲፈርስ አፈረሳቸው
አዝማች · Chorus
አፈረሳቸው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔማ ጌታን ብዬ
አላፈርኩ እርሱን ብዬ
ጨመረ ምሥጋናዬ (፪x)
ጨመረ ምሥጋናዬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ለእንቆቅልሼ መፍትሄ ሰጥቶ
የሚያስፈነድቅ የልብን ሞልቶ
ከአፉ ከወጣ ስልጣን ያለው ቃል
የማይሆን የለም ያለው ይሆናል
እንደርሱ ማነው ተዐምረኛ
እንቆቅልሼን ፈቶ አሳየኛ
ፈቶ አሳየኛ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ተሰርቶልኝ ስራዬ
ሃዘን ሄዷል ከላዬ
ቤቴን ሞላው ደስታ
ልዘምር ለዚህ ጌታ (፪x)
ልዘምር ለዚህ ጌታ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ፍጥረት በስራህ የሚገዙለት
ማዕበል ወጀቡ የሚታዘዙለት
ይናገር እንጁ ይበል ንጉሡ
ማይሰማው የለም ሕያው ግዑዙ
እርሱ ነው ጌታ ዐይኔ አይቶታል
ማይቻለውን ሁሉ ችሎታል
ሁሉ ችሎታል (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
እኔማ ጌታን ብዬ
አላፈርኩ እርሱን ብዬ
ጨመረ ምሥጋናዬ (፪x)
ጨመረ ምሥጋናዬ
ቁጥር 9 · Verse 9
ተሰርቶልኝ ስራዬ
ሃዘን ሄዷል ከላዬ
ቤቴን ሞላው ደስታ
ልዘምር ለዚህ ጌታ (፪x)
ልዘምር ለዚህ ጌታ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ