Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በአንተ ነው መኖሬ

Beante New Menorie

2008 · ትራክ 1 · 5:10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ በአንተ ነው መኖሬ (፫x)

ቢረዳልኝ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ልቤ

በአንተ ነው መኖሬ (፪x)

ለምን እፈራለሁ እንዴትስ እሰጋለሁ (፪x)

የዘለዓለም ኪዳን ከአንተ ተቀብያለሁ (፪x)

ዘመናቴን ቆጥረህ አውቀሃል እርምጃዬን (፪x)

ትላንትም አይቆጨኝ ነገም አያስፈራኝ (፬x)

ጌታ በአንተ ነው መኖሬ (፫x)

ቢረዳልኝ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ልቤ

በአንተ ነው መኖሬ (፪x)

በሕይወት መዝገብ በነፍሴ የተጻፈው (፪x)

በዓመታቶቼ ላይ ክብርህ የተገለጠው (፪x)

ድንቅ ተዓምራትህ ቃላትም የማይገልጸው (፪x)

መኖሬ እራሱ ሕያው ምስክር ነው (፬x)

ጌታ በአንተ ነው መኖሬ (፫x)

ቢረዳልኝ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ልቤ

በአንተ ነው መኖሬ (፪x)

ምህረት ቸርነትህ እየተከታተሉኝ (፪x)

የሥምህ ጉልበቱ ከሞት ስላስጣለኝ (፪x)

በዘመኔ ሁሉ ሥምህን እጠራለሁ (፪x)

በሕያዋን አገር በፊትህ እኖራለሁ (፪x)

ቤትህ እኖራለሁ (፪x)

ጌታ በአንተ ነው መኖሬ (፫x)

ቢረዳልኝ ልቤ ፣ ቢረዳልኝ ልቤ

በአንተ ነው መኖሬ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ