Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይኸው

Yehew

2008 · ትራክ 11 · 4:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከስምህ ሌላ ቀንበር አይጫነኝ

ከፍቅርህ ሌላ ዕዳ አይኑርብኝ

አምላኬ ሆይ እባክህ አግዘኝ

የእኔ ጌታ በፍቅርህ አኑረኝ (፪x)

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወደጄ ለአንተ አስገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለአንተ እኖራለሁ

የልቤን ሃሳብ መርምረህ ታውቃለህ

አረማመዴን ትመለከታለህ

እግዚአብሔር ሆይ ፍፁም ህግህ ይግዛኝ

የተሰወረ ኀጢአት እንዳይገዛኝ (፪x)

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለቃልህ እገዛለሁ

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወድጄ ልቤን አስገዛለሁ

ፍቅርህ ፍፁም ነው ነፍስን ይመልሳል

ስራትህ ልብን ደስ ያሰኛል

ልጠብቀው ለቃልህ እተጋለሁ

የዚያን ጊዜ ፍፁም እሆናለሁ (፪x)

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለቃልህ እገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ወድጄ ልቤን አስገዛለሁ

ትእዛዝህ ብሩህ ዐይንንም ያበራል

ፍራትህ ንጹህ ዘላለም ይኖራል

ከከበረ እንቁ ይመረጣል

ከማር ይልቅ እጅግ ይወደዳል (፪x)

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወድጄ ለአንተ እገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለአንተ እኖራለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወድጄ ለአንተ እገዛለሁ

ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጂ ለአንተ እኖራለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለቃልህ እገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወድጄ ልቤን አስገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ፈቅጄ ለቃልህ እገዛለሁ

ይኽው ይኽው ይኽው እራሴን እሰጣለሁ

ወድጄ ልቤን አስገዛለሁ

ይኸው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ