እኔ ግን
Enie Gen
2008 · ትራክ 6 · 3:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጽድቅን ጥሩር ለብሼ
ገነትም ጋሻ አንስቼ
በቃል እውነት ታጥቄ
እቆማለሁ ፀንቼ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ግን እግዚአብሔርን አመልካለሁ
በዘመኔ ሁሉ ለእርሱ እገዛለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በፍጹም ልቤ እሰግዳለሁ
ሃሳቤን አስገዛለሁ
በፈቃዴ እሸነፋለሁ
ጌታዬን አመልከዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ግን እግዚአብሔርን አመልካለሁ
በዘመኔ ሁሉ ለእርሱ እገዛለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በጽኑ ምክሩ ታምኜ
በቅን ስርዓቱ ሄጄ
ቅዱስ ሥሙን አከብራለሁ
አምላኬን አመልከዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ግን እግዚአብሔርን አመልካለሁ
በዘመኔ ሁሉ ለእርሱ እገዛለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔርን እባርካለሁ
ምሥጋናውም ሁሉ በአፌ ነው
በእርሱ ፍቅር አኖራዋለሁ
ዘለዓለም አመልከዋለሁ
አዝማች · Chorus
እኔ ግን እግዚአብሔርን አመልካለሁ
በዘመኔ ሁሉ ለእርሱ እገዛለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ