ማነው
Manew
2008 · ትራክ 14 · 6:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰላም አለቃ የዘለዓለም አባት
ምሥጋናና ክብር የተገባው ስግደት
ድንቅ መካር አምላክ ሃያልም ይባላል
ስልጣን አለቅነት ለእርሱ ተሰጥቶታል
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መንገድና ሕይወት እውነትም ነኝ ያለው
በዘለዓለም ዙፋን በአባቱ ቀኝ ያለው
ብርታትና ጥበብ ኃይልም የተሞላው
ክብሩ የገነነ ምሥጋናው ብዙ ነው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የክንፉ መዘርጋት ምድርን ይሸፍናል
በሰማይ ሰማያት በክብር ይራመዳል
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ ነው
በትንሳኤ በኩል የእግዚአብሔር ልጅ ነው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሲዘባበቱበት አፉን አልከፈተም
በከሳሾቹ ፊት ቆሞ አልተሟገተም
ሞትና መውጊያውን . (1) . ያስቀራል
ፍጥረት ሁሉ ለእርሱ ጉልበትም ይገዛል
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከነገድ ከቋንቋ ወገኑን ለይቷል
የሕይወትን መዝገብ ማኅተሙን ፈቷል
ነፍሱን ቤዛ ሰጥቶ ብዙዎችን ማርኳል
ከሃያላንም ጋር ምርኮን ይካፈላል
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያገለግሉት
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህ የሚሉት
ያለ የነበርነው ደግሞም ይመለሳል
ለዓለም ለዘለዓለም መንግሱ ይጸናል
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የወደደኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ማነው ማነው የማመልከው ማነው
የመረጠኝ ማነው ይህ ኢየሱስ ማነው
ለዘለዓለም አምካኬ ነው
ለዘለዓለም ጌታዬ ነው
ለዘለዓለም ለዘለዓለም ለዘለዓለም ንጉሤ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ