እንደ እኔማ ቢሆን
Endeniema Bihon
2008 · ትራክ 3 · 3:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደኔማ ቢሆን አልቆልኝ ነበረ
የበደሌ ብዛት እየተቆጠረ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ግን አምላኬ ግን ዕዳዬን አስቀረ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በዘለዓለም ሥሙ ቃልኪዳን ገባልኝ
አንቺ ልጅ በሕይወት ትኖሪያለሽ አለኝ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ነው አዳኜ ነው እኔ እወደዋለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የኃጥያቴ ቀንበር ከብዶ እያስጨነቀኝ
ከሰው ሁሉ መሃል ነጥሎ እያስቀረኝ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ግን አምላኬ ግን ፈልጐ አገኘኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ያደረኩትን ሁሉ የልቤን ነገረኝ
ኃጥያቴን ሻረና ከሰው ቀላቀለኝ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ነው ጌታዬ ነው እኔ አመልከዋለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ዳግም ላልጠማ ቀንበር ላይጫነኝ
ከጨለማው ሰፈር ጠርቶ አወጣኝ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ነው አምላኬ ነው እኔ አመልከዋለሁ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ዝም በይ አትበሉኝ እኔ ዝም አልልም
የተረደገልኝ ዝም አያሰኘኝም
ኢየሱስ ነው እርሱ እኮ ነው ለእኔ የደረሰው
አዝማች · Chorus
ጌታዬ ነው አምላኬ ነው እገዛለታለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ