ከሰማሁት በላይ
Kesemahut Belay
2008 · ትራክ 5 · 5:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላክነትህን ታላቅነትህ ጌትነትህ
ከሰማሁት በላይ ነው ከገመትኩት
ከሰማሁት በላይ ነው ከገመትኩት (፪x)
አምላኬ (፫x) እያልኩኝ
በፊትህ ብሰግድ ያለኝን ባስቀምጥ
ቃላት አላገኝም ክብርህን የሚገልጥ (፪x)
አዝማች · Chorus
መልካምነትህ አባትነትህ ደግነትህ
ከሰማሁት በላይ ነው ከገመትኩት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምህረት ቸርነትህ ተከትለውኛል
በፀጋ ላይ ፀጋ ፍቅርህ ደግፎኛል
መልካም ነህ አምላኬ በስጦታህ አትጸጸት
ቆጥሬ አልጨርስም ጌታ የአንተን ደግነት (፪x)
አዝማች · Chorus
መልካምነትህ አባትነትህ ደግነትህ
ከሰማሁት በላይ ነው ከገመትኩት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በዘመኔ ሁሉ የማውቀው እውነቱ
ቀዝቅዞ አያውቅም መውደድህ ግለቱ
የፍቅርህ ስፋቱ ልክ የለው ጥልቀቱ
በመስቀል ተገልጧል አምሳያ ማጣቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
አምላክነትህ ታማኝነትህ ወዳጅነትህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ከሰማሁት በላይ ነው ከገመትኩት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ