Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተራራውን ሰጠኝ

Terarawen Setegn

2008 · ትራክ 12 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፪x)

ትወርሻለሽ ብሎ ቃል የገባልኝ

አምላኬ የሰጠኝ ብዙ ርስት አለኝ

አቅሜ ያለቀ የደከምኩ ብመስልም

እምነቴ ብርቱ ነው አልነቃነቃም (፫x)

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፪x)

ከፍ ከፍ ብሎ አይሎ ይታያል

ኃይል ግን የለውም ጠላት ይወድቃል

እንደ እንጀራ ነው ተቆርሶ ሚበላ

ለጠላቴ ዛቻ ጉልበቴም አይላላ (፫x)

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፪x)

ሰላም በሌለበት ሰላም ነው ትላለች

ድምጿን ከፍ አድርጋ አብዝታ ዝታለኝ

እባክህ አምላኬ ውጣ ከእኔ ጋራ

ኤልዛቤልን ስጠኝ የህዝብህን . (1) . (፪x)

ስጠኝ ኤልዛቤልን የህዝብህን . (1) .

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፪x)

ባለራዕይ ደክሞ ጦረኛው ተማርኳል

እምነቱ ዝሎበት ልቡ ሸፍቷል

አስታጥቀኝ ለውጊያ አርገኝ ጦረኛ

ለፈረሰው ቅጥር ለቤትህ ጉበኛ (፫x)

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፪x)

ተዋግቶ ማሸነፍ ተለምምጃለሁ

ስለ ተስፋ ቃልህ በሕይወት እኖራለሁ

ስጠኝ ያን ተራራ አልታረሰም ገና

ለመውጣት ለመውረስ ኃይል የአንተ ነውና (፪x)

ለመውጣት ለመውረስ ጉልበቴ ነህና

ተራራውን ስጠኝ ተራራውን

ተራራውን ስጠኝ ያን ተራራ

ተራራውን ስጠን ስጠኝ

ዛሬም እንደቀድሞው ጉልበታም ነኝ

ዛሬም እንደጥንቱ እምነት አለኝ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ