ህልሜ
Helmie
2008 · ትራክ 7 · 9:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ጋራ ስሆን ሃሳቤን ጥላለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ጭንቀቴን ረሳለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ሰላሜ ሙሉ ነው
ከአንተ ጋራ ስሆን ደስታዬ ፍፁም ነው
ከአንተ ጋራ ስሆን ሃዘኔን ተዋለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ጉድለቴን ረሳለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ለሊቱም ይነጋል
ከአንተ ጋራ ስሆን ባዶዬ ይሞላል
አዝማች · Chorus
ህልሜ ፣ ህልሜ
ቁጥር 2 · Verse 2
ህልሜ ጌታ አንተ ነህ ለእኔ
ጌታ አንተ ነህ ለእኔ ኦሆሆ
ጌታ አንተ ነህ ለእኔ
ውዴ አንተ ነህ ለእኔ ኦሆሆ
ውዴ አንተ ነህ ለእኔ
ከአንተ ጋራ ሳየው ተራራው ይናዳል
ከአንተ ጋራ ሳየው ሸለቆው ይሞላል
ከአንተ ጋራ ስሆን እኔ አይላለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ጠላቴን ጥላለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ድካሜን ረሳለሁ
ክንድህን ተደግፌ በአንተ እመካለሁ
ከአንተ ጋራ ስሆን ከቶ የለኝ ከልካይ
የአባትነት ፍቅርህ ልጅነቴ ገብቶኝ
አዝማች · Chorus
ህልሜ ፣ ህልሜ
ቁጥር 3 · Verse 3
ህልሜ ጌታ አንተ ነህ ለእኔ
ጌታ አንተ ነህ ለእኔ ኦሆሆ
ጌታ አንተ ነህ ለእኔ
ውዴ አንተ ነህ ለእኔ ኦሆሆ
ውዴ አንተ ነህ ለእኔ
ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍስ ጩኸቷ
ከአንተ ጋራ መሆን ሁልጊዜ ናፍቆቷ
ፊትህን እያየሁ ጌታዬ ላመልክህ
ክብርህን እያየሁ ወድቄ ላደንቅህ
አዝማች · Chorus
ህልሜ ፣ ህልሜ
ቁጥር 4 · Verse 4
ህልሜ ውብ ፊትህን ማየቴ
ውብ ፊትህን ማየቴ አሃሃ
ዙፋንህን ማየቴ
ውብ ፊትህን ማየቴ ኦሆሆ
ክብርህን ማየቴ
ዙፋንህ ሥር ሆኜ እኔም አሰግዳለሁ
ከሰማሁት በላይ ድንቅ ነህ እላለሁ
ባልተሰማ ቅኔ ያኔ አቀኛለሁ
ከመላዕቶችህ ጋር አብሬ አሰግዳለሁ
አዝማች · Chorus
ህልሜ ፣ ህልሜ
ቁጥር 5 · Verse 5
ህልሜ ውብ ፊትህን ማየቴ
ክብርህን ማየቴ ኦሆሆ
ክብርህን ማየቴ
ውብ ፊትህን ማየቴ አሃሃ
ዙፋንህን ማየቴ
የሚጠፋው አልፎ የሚጠፋውን ስለብስ
እሩጫዬ አልቆ ዘለዓለሜ ስደርስ
ያኔ የፍቅር ፊትህን ፊት ለፊቴ ሳየው
በምን ቋንቋ ይሆን መውደዴን ምገልጸው
አዝማች · Chorus
ህልሜ ፣ ህልሜ
ቁጥር 6 · Verse 6
ህልሜ ውብ ፊትህን ማየቴ
ክብርህን ማየቴ ኦሆሆ
ክብርህን ማየቴ
ውብ ፊትህን ማየቴ ኦሆሆ
ክብርህን ማየቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ