ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጥራው
Gieta Amlakie Beyie Seteraw
2008 · ትራክ 8 · 6:01 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳልኝ ክንዱ
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳ ያ ክንዱ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠላቴ ሲከሰኝ አሃሃ ድካሜን ሲያሳየኝ ኦሆሆ
ኃይል ሆነልኝ ለእኔ እግዚአብሔር አገዘኝ (፪x)
እራሴን ቀብቶ ኦሆሆ በመቅደሱ አቆመኝ አሃሃ
እንደ መልካም እርሻ ውብ መዓዛ ሰጠኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳልኝ ክንዱ
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳ ያ ክንዱ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በደሌን ኀጢአቴን አሃሃ በደሙ አጠበና ኦሆሆ
ለእኔም አንደ ያዕቆብ ሥሜን ለወጠና
ታሪክ ቃየረና
የራሱ አደረገኝ ኦሆሆ በሥሙ ተጠራሁ አሃሃ
በቀረው ዘመኔ ልኖር አስከብሬው እንድኖር
አዝማች · Chorus
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳልኝ ክንዱ
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳ ያ ክንዱ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝማሬ የሰማ አሃሃ በባዕድ አገር ላይ ኦሆሆ
ሊያስጥለኝ ተነሳ ውዴን ከእጄ ላይ
እኔን ከእርሱ ሊለይ
እኔ ግን ተስፋዬን አሃሃ ላልረሳ ምያለሁ ኦሆሆ
ደስታዬ በጌታ እንደሆነ አውቃለሁ ተደላድያለሁ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳልኝ ክንዱ
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳ ያ ክንዱ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የአባቶቼ አምላክ አሃሃ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው ኦሆሆ
የተማመንኩበት ሥሙ እግዚአብሔር ነው
እርሱ ኤልሻዳይ ነው
እግሮቼን ጠብቆ ኦሆሆ ኃይልን አስታጥቆኛል አሃሃ
በከፍታዎቹ በክብሩ አራምዶኛል በድል አቁሞኛል
አዝማች · Chorus
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳልኝ ክንዱ
ጌታዬ አምላኬ ብዬ ስጠራው
ከቅዱስ ማደሪያው ተነሳ ያ ክንዱ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ