Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሳቅ አድርጐልኛል

Saq Adergolegnal

2008 · ትራክ 10 · 5:11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳቅ ሳቅ (፪x) ሳቅ አድርጐልኛል

ሳቅ (፫x) ሳቅ በሳቅ ሆኖልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ፈቃዱን ፈጽሞልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ኪዳኑን አጽንቶልኛል (፪x)

በልቤ ሞልቶ ሃዘኔን ወስዶ

ጠላቴን ጥሎ ወዲያ አባሮ

ሞላልኝ መሻቴ ደስ አለኝ በአምላኬ

ሰጠኝ እንደልቤ ደስ አለኝ በአምላኬ (፪x)

ሳቅ ሳቅ (፪x) ሳቅ አድርጐልኛል

ሳቅ (፫x) ሳቅ በሳቅ ሆኖልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ፈቃዱን ፈጽሞልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ኪዳኑን አጽንቶልኛል

ተጣልኩኝ ልሞት ሊያጠፋኝ ጠላት

ገባሁኝ ለግዞት ያሰረኝ መስሎት

ዘመን ሲመጣ ቀኑ ሲገለጥ

የተከሰስኩበት/ተታማሁበት) ሆነልኝ ለሹመት (፪x)

ሳቅ ሳቅ (፪x) ሳቅ አድርጐልኛል

ሳቅ (፫x) ሳቅ በሳቅ ሆኖልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ፈቃዱን ፈጽሞልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ኪዳኑን አጽንቶልኛል

አይችልም አልልም እግዚአብሔር ትልቅ ነው

አይሆንም አልልም ሆኖልኝ እያየሁ

አጋጣሚ አይደለም ወይ የሰው ነገር

የማይሰማ የለም እግዚአብሔር ሲናገር (፪x)

ሳቅ ሳቅ (፪x) ሳቅ አድርጐልኛል

ሳቅ (፫x) ሳቅ በሳቅ ሆኖልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ፈቃዱን ፈጽሞልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ኪዳኑን አጽንቶልኛል (፪x)

አምላኬ አስቦልኛል ፈቃዱን ፈጽሞልኛል

አምላኬ አስቦልኛል ኪዳኑን አጽንቶልኛል (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ