Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለእርሱ ክብር ይሁን

Lersu Keber Yehun

2006 · ትራክ 2 · 5:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለሚታመኑበት ተስፋ ላደረጉት

በጊዜው ደርሶ ማሳረፍን ያውቃል

እግዚአብሔር አይዋሽም ለቃሉ ይተጋል

ለእርሱ ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ማንም የለም

አሜን ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

ቢቆይ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም

ኦሆ ለልዑል እግዚአብሔር (፪x)

በሠማይ በምድር ክብር ይሁን ክብር (፪x)

አሜን ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ማንም የለም

እሰይ ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

ቢቆይ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም

እንደ ትላንትናው ዛሬም ድንቅ ሊሰራ

ኤልሻዳይ ነው እርሱ የሚያቅተው የለም

ክንዱ አልደከመም ብርቱ ነው ዘለዓለም

ለእርሱ ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ማንም የለም

አሜን ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

ቢቆይ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም

ፅድቅን የሚወደው እግዚአብሔር ፃድቅ ነው

ፍርድንም አያዛባም ማዳላት አያውቅም

ሚዛኑ ትክክል እርሱ አይሳሳትም

ለእርሱ ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ማንም የለም

አሜን ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

ቢቆይ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም

ኦሆ ለልዑል እግዚአብሔር (፪x)

በሠማይ በምድር ክብር ይሁን ክብር (፪x)

አሜን ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ማንም የለም

እሰይ ክብር ይሁን ክብር ዘለዓለም (፪x)

ቢቆይ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ