Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ውዴ የእኔ ነው

Wedie Yenie New

2006 · ትራክ 3 · 7:10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

አልተሳሳትኩም እኔ በምርጫዬ

ከሞት ሕይወት ይሻላል ብዬ

ነፍሴን ሊታደግ በሩን ላንኳኳው

ከፈትኩለት ልቤን ኢየሱሴን ላስገባው

እርሱም አሜን ሕይወቴን ወረሰው

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

ሞልቶልኝ ከማጣ ኢየሱሴን

አልፈልግም መርጣለሁ ሞቴን

ፍቅሩን ቀምሼ ወዴት ሄዳለሁ

ልለየው አልችልም እጅግ ወደዋለሁ

ከእርሱ የተነሳ ከሞት ድኛለሁ

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

አይለወጥም እንደ ሰው አይደለም

አምነዋለው ኢየሱስ አይከዳኝም

በዘለዓለም ፍቅሩ ስቦኛል ወዶኛል

እስከ ሽበት ቢሆን እርሱ ይሸከመኛል

ሰልችቶ ውዴ መቼ ይጥለኛል

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

ውርደቴን በክብር ለውጦልኝ

የማዳንን ልብስ አለበሰኝ

የባርነቴም ቀንበር ሰብሮልኝ

ቀና ብዬ እንድሄድ ኢየሱስ አደረገኝ

እሰይ ለዘለዓለም ይንገስልኝ

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

ከምንም በላይ አዎ የሚበልጠው

ታማኙ ኢየሱስ ባልንፈራዬ ነው

ቃሉ ይጣፍጣል ልብን ይደርሳል

ውዴ እኮ ልዩ ነው ማንስ ይመስለዋል

ምርጫዬ ነው እርሱም እኔን መርጧል

ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (፪x)

ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ

ኢየሱሴን አትንኩብኝ

በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ

እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ

አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው

አላማውም ፍቅር ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ