ማንም የለም
Manem Yelem
2006 · ትራክ 12 · 6:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማንም የለም ከአንተ በቀር (፪x)
የውስጤን የልቤን የሚረዳ ሚያጽናና
አንተ ብቻ የእኔ ጌታ
ጋሻ ነህ መከታ አሃሃ
አንተ ብቻ መጠለያ
ጥላ ነህ ከለላ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰውማ ሰው ነው ያው እንደተፈጥሮ
ድጋፍን ረዳትን ፈላጊ ነው ምርኩዝን
ስለዚህ ወደ አንተ መጠጋት ያዋጣል
የታመነ አንተን ድል በድል ይሆናል
አዝማች · Chorus
ማንም የለም ከአንተ በቀር (፪x)
የውስጤን የልቤን የሚረዳ ሚያጽናና
አንተ ብቻ የእኔ ጌታ
ጋሻ ነህ መከታ አሃሃ
አንተ ብቻ መጠለያ
ጥላ ነህ ከለላ
ቁጥር 2 · Verse 2
ልብን ኩላሊትን ትመረምራለህ
የሰውን ሁለንተና አንተ ብቻ ታውቃለህ
በቅን የሚፈርድ አንደአንተ ማን አለ
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ኤልሻዳይ ጌታ ነህ
ጉልበቴ ዝማሬዬ ጌታዬ ኤሄሄ
ጉልበቴ ዝማሬዬ የሱሴ
አንተን ወዳ ትባርክሃለች ነፍሴ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማንም የለም ከአንተ በቀር (፪x)
የውስጤን የልቤን የሚረዳ ሚያጽናና
አንተ ብቻ የእኔ ጌታ
ጋሻ ነህ መከታ አሃሃ
አንተ ብቻ መጠለያ
ጥላ ነህ ከለላ
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀን በደመና አምድ መምራትን ታውቃለህ
ሌሊትም በእሳት ጌታ ትመራለህ
ልዩ ነው ስራህ ግሩም ጥበቃህ
ተመስገን ተባረክ ከፍ በል ልበልህ
አዝማች · Chorus
ማንም የለም ከአንተ በቀር (፪x)
የውስጤን የልቤን የሚረዳ ሚያጽናና
አንተ ብቻ የእኔ ጌታ
ጋሻ ነህ መከታ አሃሃ
አንተ ብቻ መጠለያ
ጥላ ነህ ከለላ
ቁጥር 4 · Verse 4
የምታስመካ ጌታ የምታኮራ ሆሆሆሆ
የምታስመካ ጌታ የምታኮራ አሃ (፪x)
ጉልበቴ ዝማሬዬ ጌታዬ
ጉልበቴ ዝማሬዬ የሱሴ
አንተን ወዳ ትባርክሃለች ነፍሴ (፪x)
ጉልበቴ ዝማሬዬ ጌታዬ
ጉልበቴ ዝማሬዬ የሱሴ
አንተን ወዳ ትባርክሃለች ነፍሴ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ