Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ብቻ ታማኝ ነው

Gieta Becha Tamagn New

2006 · ትራክ 8 · 3:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በዓለም ላይ ቢዞር ቢዞር

አይገኝም ያለ እንደ እግዚአብሔር

መደነቅ መገርም ሞላብኝ

አምላኬን ሳስበው ደስ አለኝ (፪x)

ጌታ ብቻ (፬x)

ጌታ ብቻ ታማኝ ነው (፫x)

ትናንትና ዛሬም ለዘለዓለም

በጥላ መዘዋወር አያውቅም

ታማኝ እንደሆነ ይኖራል

የሚታመኑትን ያኮራል (፪x)

እርሱ ብቻ (፬x)

እርሱ ብቻ ታማኝ ነው (፫x)

የሚከፍት ሚዘጋ የሌለው

ሚዘጋም የሚከፍትም የሌለው

ሁሉን ማድረግ ፍጹም የቻለ

እንደ ኢየሱስ ያለ ማን አለ (፪x)

ኢየሱስ ብቻ (፬x)

ኢየሱስ ብቻ ጌታ ነው (፫x)

እርሱ ብቻ አዳኝ ነው (፫x)

ጌታ ብቻ ታማኝ ነው (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ