አበርትቶኛል
Abertetognal
2006 · ትራክ 1 · 5:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አበርትቶኛል ጉልበቴ እጅግ ዝሎ
አሻግሮኛል ዮርዳኖስን ከፍሎ
እንዴት እረሳዋለሁ እግዚአብሔርን
ከበረት አውጥቶ ከግብጽ ያወጣኝን
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት
በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አስቀድሞ አውቆኛል በሆድ ሳልሰራ
መርጦኛል እራሱ ጨለማዬም በራ
ዓይኖቼም ማዳኑን እዩ ተዓምራቱን
ስለ ፍቅርም ብሎ የሰዋውን ልጁን
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት
በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አስጨናቂዎቼ ሰልፍ አብዝተውብኝ
ከአምላኬ ጉያ መስሏቸው የሚነጥቁኝ
ግን የማያንቀላፋው ተግቶ የሚጠብቀኝ
በዙሪያዬ ካሉት በእውነት አሳረፈኝ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት
በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር ፍቅር ነው በፍቅሩ ይዞኛል
እንዳልወድቅም ምርኩዝ ድጋፍ ሆኖልኛል
ምን ልበለው እኔስ ውለታው በዛብኝ
ሕያዋን ሁላችሁ እስኪ አመስግኑልኝ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት
በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ