Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሳላቋርጥ አመሰግንሃለሁኝ

Salaquaret Amesegenehalehugn

2006 · ትራክ 14 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳላቋርጥ አመሰግንሀለሁኝ አመሰግንሀለሁኝ (፪x)

ከአንተ ብዙ ብዙ ብዙ ተቀብያለሁኝ አመስግንሀለሁኝ

ሁሉ ከአንተ ሁሉ በአንተ ሁሉ ደግሞ ለአንተ ነውና አሃ

ይሄው ምሥጋና

እንደ ወደድከኝ ወድጀሃለሁ

ንጉሥ ሆይ ንገሥ ንገሥ አላለሁ

እንዳከበርከኝ አከብርሃለሁ

ባርኮቴ ሆይ እባርክሃለሁኝ (፬x)

ሳላቋርጥ አመሰግንሀለሁኝ አመሰግንሀለሁኝ (፪x)

ከአንተ ብዙ ብዙ ብዙ ተቀብያለሁኝ አመስግንሀለሁኝ

ሁሉ ከአንተ ሁሉ በአንተ ሁሉ ደግሞ ለአንተ ነውና አሃ

ይሄው ምሥጋና

እንዳልተቀበለ እንዴት እሆናለሁ

ማዳንህን እኔ እኔ አይቻለሁ

ባለውለታዬ ክበር እላለሁ

አንተኑ ብቻ እባርክሃለሁኝ) (፬x)

ሳላቋርጥ አመሰግንሀለሁኝ አመሰግንሀለሁኝ (፪x)

ከአንተ ብዙ ብዙ ብዙ ተቀብያለሁኝ አመስግንሀለሁኝ

ሁሉ ከአንተ ሁሉ በአንተ ሁሉ ደግሞ ለአንተ ነውና አሃ

ይሄው ምሥጋና

ረዳቴ ሆይ እኔ ላንተ እዘምራለሁ

ገና ለክብርህ ለክብርህ ሮጣ ለሁ

ለጠላቴ ሽንፈት ድልን አውጃለሁ

በምሥጋና አንተን እባርክሃለሁኝ (፬x)

ሳላቋርጥ አመሰግንሀለሁኝ አመሰግንሀለሁኝ (፪x)

ከአንተ ብዙ ብዙ ብዙ ተቀብያለሁኝ አመስግንሀለሁኝ

ሁሉ ከአንተ ሁሉ በአንተ ሁሉ ደግሞ ለአንተ ነውና አሃ

ይሄው ምሥጋና

ስላደረክልኝ ምን እመልሳለሁ

ታምራትህ ብዙ ብዙ እኮ ነው

በወንድሞች መካከል ስምን እጠራሃለሁ

ኢኢየሱስ ሆይ እባርክሃለሁ (፪x)

ሳላቋርጥ አመሰግንሀለሁኝ አመሰግንሀለሁኝ (፪x)

ከአንተ ብዙ ብዙ ብዙ ተቀብያለሁኝ አመስግንሀለሁኝ

ሁሉ ከአንተ ሁሉ በአንተ ሁሉ ደግሞ ለአንተ ነውና አሃ

ይሄው ምሥጋና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ