ምንም በሌለበት
Menem Belielebet
2006 · ትራክ 4 · 5:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምንም በሌለበት ጭው ባለው በረሃ
አጋር ከነልጇ ወደዚያ ተሰዳ
ተደፍታ ስታለቅስ ምርር ያለ ለቅሶ
ምንጭ አፈለቀላት እግዚአብሔር ደርሶ [1]
አዝማች · Chorus
ይደርሳል እግዚአብሔር ይደርሳል
ይደርሳል የተጠማ ያያል
ምንጭን ያፈልቅና አሜን ያሳርፋል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መጠጥ እነደጠጣች ስካር እንደያዛት
ካህኑ ኤሊ እንኳን ሃናን ጠረጠራት
እርሷ ግን የውስጧን ችግሯን ለሚያውቀው
ተናገረችና ልቧ በእርሱ ፀና [2]
አዝማች · Chorus
ይረዳል እግዚአብሔር ይረዳል
ይረዳል የውጥን ይረዳል
የተዘጋን ከፍቶ በልጅ ይባርካል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስራኤላውያኖች ቀንበር ከብዶባቸው
የግብፅ ባርነት እጅግ ሰልችቷቸው
ጮሁ ወደ እግዚአብሔር እንዲታደጋቸው
እጁን ዘረጋና ነፃ አወጣቸው [3]
አዝማች · Chorus
ያወጣል እግዚአብሔር ያወጣል
ያወጣል ነፃነት ይሰጣል
ከእስራት ይፈታል አሜን ያሳርፋል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እመሰክራለሁ በሕይወቴ አይቻለሁ
ንብ ማርን እንዲከብ ተከብቤ ሳለሁ
በጨነቀኝ ጊዜ አምላኬን ስጣራ
እርሱም ደረሰልኝ ጨለማዬም በራ
አዝማች · Chorus
ያበራል እግዚአብሔር ያበራል
ያበራል ጨለማን ይገፋል
በድንቅ ይደርስና አሜን ያሳርፋል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ቀን በደመና አምድ ለሊትም በእሳት
አቤት የእኔ ጌታ መምራትን ሲያውቅበት
ላዘነው መፅናናት ለደካማው ብርታት
ይሄ ነው አምላካችን እስኪ ዕልል በሉለት
አዝማች · Chorus
ይብዛለት አሁንም ይብዛለት
ይብዛለት ምሥጋና ይብዛለት
አሜን ለአምላካችን ክብር ይሁንለት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ