Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስለተደረገልኝ በጐነት

Seletederegelegn Begonet

2006 · ትራክ 5 · 5:48 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለተደረገልኝ በጐነት

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (፪x)

ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)

አመሰግንሃለው (፮x)

እንደ ባለማዕረግ ሰው ተመልክተኸኝ

የማይገባኝን ክብርን ሰጥተኸኝ

የርስትህ ተካፋይ የአንተው አደረከኝ

ለዚህ ልታበቃኝ ታዲያ እኔ ማን ነኝ (፪x)

ስለተደረገልኝ በጐነት

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (፪x)

ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)

አመሰግንሃለው (፮x)

ማዕበሉ በዝቶብኝ እኔን ሲያንገላታኝ

ጌታ ኢየሱስ አልኩኝ ሥምህን ጠራሁኝ

እጅህን ዘርግተህ በፀናችው ክንድህ

ታደከኝ አዳንከኝ ተባረክ ልበልህ (፪x)

ስለተደረገልኝ በጐነት

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (፪x)

ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)

አመሰግንሃለው (፮x)

የተገለጠውን ፍቅርህን እያየሁ

እንዳልተቀበለ እንዴት እሆናለሁ

ምህረት ማዳንህን ሁሌ አወራለሁ

አምላኬ እንደ አንተ ፍፁም አምላክ ማነው (፪x)

ስለተደረገልኝ በጐነት

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (፪x)

ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)

አመሰግንሃለው (፮x)

በለቅሶ ሸለቆ በወሰንከው ስፍራ

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ በረከትህ በዛ

ከኃይል ወደ ኃይል ያሸጋገርከኝ

ሁሉ በአንተ ሆነልኝ ኧረ ምን ጐደለኝ (፪x)

ስለተደረገልኝ በጐነት

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው

ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (፪x)

ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)

አመሰግንሃለው (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ