ነገር ለብጐ
Neger Lebego
2006 · ትራክ 13 · 4:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ደመና ሆኖብኝ ሁሉ ነገር ጨልሞብኝ
ዐይኖቸን አቅንቸ ጌታዬ ሆይ ፍረድልኝ አልኩኝ
(ለካ ደመናው ውኃ ያዘለ ነበር
ደረቀ ባልኩበት ዝናቡ ወረደበት) (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር ለበጐ ሆኖ አየሁኝ ነገረ ለበጐ (፪x)
እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ
ምረቱን ለእኔ አውርዶ
እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ
ምረቱን ለእኔ አግንኖ
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈተናው አዝሎኝ ለመውደቅም ስንገዳገድ
ባሕሩን ሲከፍለው በወጀብ ውስጥ አገኘሁኝ መንገድ
አምላክ እንደሌለው እንደማንም ለቆጠረኝ
የምመስክረው ምናገረው አለኝ (፪x)
ብቻውን ታምራት ድንቅ ሚያደርግ ነው
እኔስ አምላክ አለኝ ሁሉ የተቻለው
ብቻውን ታምራት ድንቅ ሚያደርግ ነው
እኔስ ጋሻ አለኝ ሁሉ የምተማመነው
የምተማመነው ተስፋ የማደርገው
ነገሬን በጊዜው ውብ አርጐ ስሪ ነው
ያማልክቶቻ አምላክ እምላኬ ኃይለኛ ነው
በዘመናት መሃል ጉልበቱ ያልዛለው
ቅን ይፈርዳል ለተጠጋው በጊዜው ደርሶ
ማባበልን ያውቃል የፈሰሰን እንባን አብሶ
የእኔ ጌታ ለአኔ ምርኮዬን መልሶ
እንደገና አቆመኝ ጉልበቴን አድሶ
የእኔ ጌታ ለእኔ ምርኮዬን መልሶ
እንደገና አቆመኝ ሕይወቴን አድሶ
አዝማች · Chorus
ነገር ለበጐ ሆኖ አየሁኝ ነገረ ለበጐ (፪x)
እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ
ምረቱን ለእኔ አውርዶ
እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ
ምረቱን ለእኔ አግንኖ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ