አመሰግነዋለሁ
Ameseginewalehu
አማርኛ
አዝማች · Chorus
አይነስ አምልኮ አይነስ ክብር
ድንቅን ላደረገ ለእግዚአብሔር
አይነስ ውዳሴ አይነስ ምስጋና
እስከ ዛሬ ድረስ ረድቶኛልና
ቁጥር 1 · Verse 1
መድኃኒቴ ጌታ ኢየሱስ ብርሃኔ
ወገግታዬ ሆኖ በሱ በርቷል ቀኔ
መንገዴን አቅንቷል ቀድሞልኝ ከፊቴ
ድንቅ አድርጎልኛል ይብዛለት ባርኮቴ
አመሰግነዋለሁ በሕይወት ዘመኔ
አመሰግነዋለሁ ድንቅ አድርጎልኛል
አመሰግነዋለሁ በጠላቶቼ ፊት
አመሰግነዋለሁ ድልንም ሰጥቶኛል
አዝማች · Chorus
አይነስ አምልኮ አይነስ ክብር
ድንቅን ላደረገ ለእግዚአብሔር
አይነስ ውዳሴ አይነስ ምስጋና
እስከ ዛሬ ድረስ ረድቶኛልና
ቁጥር 2 · Verse 2
እግሬን ከስብራት ዓይኖቼን ከዕንባ
ላሻገረኝ ሁሉን ጣልቃ እየገባ
በመከራው ቀኔ የሆነልኝ ተገን
በሕይወት ያኖረኝ እግዚአብሔር ይመስገን
እግዚአብሔር ይመስገን*2
እናገረውም ዘንድ የአምላኬ ምስጋና
ጌታ በሕይወቴ ድንቅ አደረገና
በደስታ ለውጦት የሐዘን ምዕራፌን
በመዝሙር ከፍታለሁ በምስጋና አፌን
ቁጥር 3 · Verse 3
ይብዛለት ምስጋና ይብዛለት ክብር
ሁሉ ላድረገ ለእግዚአብሔር
ይብዛለት ምስጋና ይብዛለት ክብር
ድንቅን ላደረገ ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ