አይቀልብኝ
Aykelibigne
አማርኛ
አይቀልብኝም አይቀልብኝም
አይቀልብኝም የእሱ ውለታ
ትውስ ይለኛል ትውስ ይለኛል
ትውስ ይለኛል የእሱ ውለታ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ
ሰንሰለቴን ጣለው እስራቴን ፈታ
በጨነቀኝ ሰዓት ደረሰልኝ ጌታ
ያደረገልኝን የማዳኑን እያየሁ
ውለታውን እያሰብኩ አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
ሰው ግራ ቢጋባ ቢሆንበት ትንግርት
እርሱን በማምለኬ ቢበዛብኝ ትዝብት
ከሆንኩለት በላይ ገና እሆናለሁ
ውለታው በሕይወቴ በዝቶልኝ ስላየሁ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ
መድኃኒት ሆነልኝ ሐዘኔን እንድረሳ
በምሕረቱ ሻረው የኃጢአቴን ጠባሳ
ኢየሱስ ባያገኘኝ እንዴት እሆን ነበር
ባለውለታዬ ጌታ ስሙ ይክበር
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
ሕይወቴን ሲያስመርር ፈተናዬ በዝቶ
ተስፋ ሲያስቆርጠኝ ሐዘኔ በርትቶ
ምሕረቱ አከመኝ በፍቅሩ ተጽናናሁ
የእርሱ መልካምነት መንገዴን አቀናው
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
በጌታ ቸርነት ነው እዚህ የደረስኩኝ
ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ
የኢየሱስ ፍቅር ነው በሕይወት ያኖረኝ
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ