ክርስቶስ
Kiristos
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከላይ የወረደ የተሰጠን ከአብ
ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ጥበብ
መንፈስ ቅዱስ ያስረዳው ለሰው የገለጠው
ጌታ ኢየሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው
አዝማች · Chorus
ክርስቶስ ኢየሱስ ሕያው
የእግዚአብሔር ልጅ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአብርሃም በፊት የነበረ
ዓለማትን በቃል ብቻ የፈጠረ
የለውም ፍፃሜ ለትውልዱ ቁጥር
ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ምስጢር
ቢወለድም እንኳ ከድንግል ማርያም
ልጄ እርሱ ነው ብሏል አብ ከአርያም
ወዶታል አባቱ በእርሱ ብሎት ደስ
የእግዚአብሔር ልጅ ነው ክርስቶስ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
ክርስቶስ ኢየሱስ ሕያው
የእግዚአብሔር ልጅ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ጸጋ እውነት ተሞልቶ ቃል በኛ ማደሩ
ይህን ሥጋና ደም አይችሉት ሊያብራሩ
ተጥሏል በዚህ የአዲስ ኪዳን መሠረት
በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ሕያው ዓለት
የቤተ ክርስቲያን ራስ በኩር የፍጥረት
የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ መለኮት
አዝማች · Chorus
ክርስቶስ ኢየሱስ ሕያው
የእግዚአብሔር ልጅ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ