ያየ ይናገር
Yaye Yinager
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አድርገህልኛል አመሰግናለሁ*2
ምሕረትህ ብዙ ነው አመሰግናለሁ
ይቅርታህ ብዙ ነው አመሰግናለሁ
ምስጋና ክብር ይብዛልህ ውዳሴ
በምሕረትህ ድናለች ነፍሴ
በጽድቅ መራኸኝ ገለል አድርገኸው አጥፊውን ከመንገዴ
ርስቴን አስውበህ በአማረ ስፍራ ላይ ወደቀ ገመዴ
ቀና አደረከኝ የሚያሳድዱኝን ከሳሾቼን ጥለህ
ላመስግንህ ጌታ ቆምኩኝ በምሕረትህ ዕድሜዬን ቀጥለህ
አዝማች · Chorus
ያየ ይናገር ያየ ይመስክር ምሕረትህን
ያየ ይናገር ያየ ይመስክር ቸርነትህን
እናገራለሁ እመሰክራለሁ
ታምራትህን በዓይኔ ስላየሁ
እናገራለሁ እመሰክራለሁ
ድንቅ ሥራህን በዓይኔ ስላየሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሞትኩኝ ነበርኩኝ ከአንተ የተለየሁ በበደል በኃጢአቴ
መሐሪ ነህ እግዚአብሔር አነሣኸኝ ዳግም መጥተህ ወደ ቤቴ
ፍቅርህ ትልቅ ነው ለእኔ ያለህ መውደድ አያልቅም ቢወራ
አዳንከኝ በጸጋ ሕይወትን ሰጥተኸኝ ከክርስቶስ ጋራ
አዝማች · Chorus
ያየ ይናገር ያየ ይመስክር ምሕረትህን
ያየ ይናገር ያየ ይመስክር ቸርነትህን
እናገራለሁ እመሰክራለሁ
ታምራትህን በዓይኔ ስላየሁ
እናገራለሁ እመሰክራለሁ
ድንቅ ሥራህን በዓይኔ ስላየሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ