Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተይዛለሁ

Teydzalehu

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቅኔ ላጫውትህ እውነቱን እናውጋ

የመወደዴን ልክ የፍቅርህን ዋጋ

የትኛውም ሆሄ ቋንቋና ሰዋሰው

አይችልም በጭራሽ ፍቅርህን ሊገልጸው

ሸፍኖታል ፍቅርህ የበደሌን ብዛት

የዘመኔን እርቃን የነፍሴን እርዛት

ኃጢአቴ ተሽሯል የለብኝም ሐፍረት

ወደ አንተ ለመቅረብ አግኝቻለሁ ድፍረት

አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ

በፍቅርህ ስለያዝከኝ አመሰግናለሁ

የፍቅርህ አሻራ በልቤ ታትሞ

ስለ ነገ ልቤ አይሰጋም ፈጽሞ

ከቶ አይናወጥም በከበበው ማዕበል

ተማምኖብህ ያድራል በስጋት መካከል

የአንተ አድርጎኛል ፍቅርህ አሸንፎ

እድፋሙን ጥምጣም ከላዬ ላይ ገፎ

ሙላት ሆኖልኛል አያሻኝም ሌላ

በፍቅርህ ኖራለሁ ከአንተ ጋር በተድላ

ማዕበሉ ቢያይል ሕይወቴን ሊያሰጥም

ፍቅርህ መልሕቄ ነው ከቶ አልናወጥም

ምንም አይነካኝም የአንተን ፍቅር አልፎ

እንዳልሰናከል ይዞኛል ደግፎ

ተይዣለሁ በፍቅርህ እኔ አልሰጋም(4*)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ