ያስመካል
Yasmekal
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታን ተስፋ ያረጉ መቼም አያፍሩም*2
ጌታን የተደገፉ መቼም አይወድቁም*2
አዝማች · Chorus
ያስመካል ያስመካል ምስክር ነኝ ያስመካል
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓይኔን አላነሣም አጋዥ ፍለጋ
ረድዔቴ አንተ ሰማይ ምድርን የሠራህ
አታሳፍረኝም ሁሉን ትችላለህ
ለጥያቄዬ ሁሉ ኢየሱስ መልስ አለህ
ጌታን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
ያስመካል ያስመካል ምስክር ነኝ ያስመካል
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ሰው ያይደለ የማያጥፍ ቃሉን
ልመናዬን ሰምቶ የሚሰጠኝ ሁሉን
ሳንኳኳ የሚከፍት ስጠይቅ ሚመልስ
ማልሰጋበት ተስፋዬ ነው ጌታዬ ኢየሱስ
ጌታን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
አዝማች · Chorus
ያስመካል ያስመካል ምስክር ነኝ ያስመካል
ቁጥር 5 · Verse 5
ይረሳናል ብለው ሳይፈሩ ሳይሰጉ
እግዚአብሔርን ተስፋ ያደረጉ
አያሳፍራቸው አይተዋቸው ከቶ
በፍጹም አያውቅም ማንንም እረስቶ
ጌታን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
ቁጥር 6 · Verse 6
ጌታን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
ኢየሱስን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
ኢየሱስን ተደግፎት ማንስ አፈረበት
ቀና ቀና ቀና አለ በስሙ ያመነ*
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ