ይታይ
Yita
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይሰወር እንግዳ ነገር አድርግና
ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ
ይታይ እጅህ በእኔ ላይ
ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ
ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ
ቁጥር 2 · Verse 2
የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ
ጌታ ሆይ በሙላት በልቤ ላይ ይፍሰስ
ለአይሁድ ለግሪክ ሰው ለጨዋ ለባሪያ
እንድሆን አድርገኝ ወንጌልን ማብሰሪያ
በምልክቶች በድንቅ ነገር
በልዩ ልዩ የአንተ ተአምር
በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት
ጌታ ሆይ ክብርህ ይታይ በእኔ ሕይወት
ቁጥር 3 · Verse 3
ከልቤ መሻት ከቃሌም በላይ
ማዳንህ ደምቆ ክብርህም ይታይ
ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ
ይታይ እጅህ በእኔ ላይ
ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ
ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሕይወቴ ብርሃን በሁሉ ፊት ይብራ
እንዳለህ ይታወቅ አንተ ከእኔ ጋራ
ይሁን መላ ሕይወቴ በክብርህ ሙሉ
አትደበቅ ከቶ ይይህ ያየኝ ሁሉ
በምልክቶች በድንቅ ነገር
በልዩ ልዩ የአንተ ተአምር
በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት
ጌታ ሆይ ክብርህ ይታይ በእኔ ሕይወት
ከልቤ መሻት ከቃሌም በላይ
ማዳንህ ደምቆ ክብርህም ይታይ
አዝማች · Chorus
ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ
ይታይ እጅህ በእኔ ላይ
ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ
ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ
ቁጥር 5 · Verse 5
እስካይቻል ድረስ ፍጹም ለመሸሸግ
በሐዋርያቱ እጅ ተአምርን ስታደርግ
እንደተደነቀ ሕዝቡ ክብርን አይቶ
በእኔም ክብርህ ይታይ አይሸሸግ ከቶ
በእኔም ክብርህ ይታይ አይሰወርም ከቶ
በእኔም ክብርህ ይታይ አይደበቅ ከቶ
በእኔም ክብርህ ይታይ አይሸሸግ ከቶ
በእኔም ክብርህ ይታይ አይሰወር ከቶ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ