Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከፀሐዩ በላይ

Ketsehayu Belay

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከፀሐዩ በታች በሚታየው ዓለም

ሁሉ እንደወትሮው ነው አዲስ ነገር የለም

ድግግም ነው አዙሪቱ

ዞሮ ይመጣል የትናንቱ

ከፀሐዩ በላይ አለ አዲስ ነገር

ያለና የነበረው የሚኖረው ትልቁ እግዚአብሔር

አሁንም ቅድምም ዛሬም ትናንትና

በማያረጅ ክብር በማይከስም ዝና

ደምቆ ይኖራል ጌታ ለዘለዓለም

በሰማይ በምድር የሚመስለው የለም

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት አምላክ

በሰማይ የሚኖር ከፍ ያለ ያለ ልክ

ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚያበራ ደምቆ

ገናና ነው እርሱ አይጨረስ ታውቆ

በሰማይ ከፍ ያለ

ኃያል አምላክ አለ

የማይቀየር ለአፍታ ከቶ

ለዘላለም ሚኖር ጸንቶ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ