ስሙን ቀደሰ
Simun Qedese
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይሆን ነገር ሆነልኝ
የማይቻለውን አስቻለኝ
እግዚአብሔር በሕይወቴ ስሙን ቀደሰ
የነገሥታትን ትጥቅ ወገብ ሊፈታ
በሮቹን ሊከፍት ሰባሪው ጌታ
ቀኝ እጄን ይዞ እንደ ቂሮስ
ከፊቴ ቀድሞ ሆነኝ ሞገስ
ሰብሮት ከፊቴ የናሱን በር
ማለፍ ሆኖልኛል በድል መሻገር
ተራራውን ናደ አረገው ሜዳ
ድንቅ አድርጎ እኔን ረዳ
አዝማች · Chorus
[ክብር ለስምህ ይሁን ክብር] 4
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ አፈራርሶ የሐማን ሴራ
ሕዝቡን ለማዳን ተአምርን ሠራ
በእኔም ሕይወት ጌታ ተገልጦ
ስሙን ቀድሷል ነገር ገልብጦ
የማይቻል ነገር ለሰው የተሳነ
ኃይልን በሚሰጠኝ በሱ ለኔ ሆነ
ከኔ ጋር መሆኑ እሱ ነው ስኬቴ
በረከት ሆነልኝ ገብቶ ወደ ቤቴ
አዝማች · Chorus
[ክብር ለስምህ ይሁን ክብር] 4
ቁጥር 3 · Verse 3
ማይመረመር የማይቆጠር
ያደርጋል ጌታ ድንቅ ታምር
ባለቀ ሰዓት ከተፍ ይልና
በሳቅ ይሞላል በድል ምስጋና
አዝማች · Chorus
[ክብር ለስምህ ይሁን ክብር] 4
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ