Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወጥቷል ከፊቴ

Wottual Kefitie

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ወጥቷል ከፊቴ ወጥቷል ከፊቴ

ኢየሱስ አባቴ ወጥቷል ከፊቴ

ስሙ ወጥቷል ከፊቴ ወጥቷል ከፊቴ

ኢየሱስ አባቴ ወጥቷል ከፊቴ

የኑሮዬ ደጀን የቤቴ ጉልላት

የእኔ ብርቱ አፍቃሪ የጠላቴ ጠላት

የነፍሴ ጠባቂ የእኔ ባላደራ

ከፊቴ ስትወጣ ማንንም አልፈራ

አለ በክፉ ቀን ጥላ

አለ መጠጊያ ከለላ

አለ መጠለያ ዋርካ

አለ አዳኝ እሚያስመካ

ጌታ ወጥቷል ከፊቴ ወጥቷል ከፊቴ

ኢየሱስ አባቴ ወጥቷል ከፊቴ

ስሙ ወጥቷል ከፊቴ ወጥቷል ከፊቴ

ኢየሱስ አባቴ ወጥቷል ከፊቴ

የማደርገው ጠፍቶኝ መሽቶብኝ በቀትር

ረድዔት ፍለጋ ዙሪያ ገብ ሳማትር

ብርሃን አበራልኝ በሕይወቴ በርቶ

ስሙን አከበረ በእኔ ታሪክ ሠርቶ

አለ በክፉ ቀን ጥላ

አለ መጠጊያ ከለላ

አለ መጠለያ ዋርካ

አለ አዳኝ እሚያስመካ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ