Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እልልታ

Elilita

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ

እልልታ ጠላቴን ለመታ

እልልታ ሕያው ላረገኝ

እልልታ ከሞት ላዳነኝ

በእኔና ሞት መሐል ቀርቶ አንድ ስንዝር

ውድቀቴን ስጠብቅ በጭንቀት ሳጣጥር

ከአዳኙ አመለጥሁ እንደ ወፍ በርሬ

ለአዳኜ አበዛለሁ ምስጋና ዝማሬ

እልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ

እልልታ ጠላቴን ለመታ

እልልታ ሕያው ላረገኝ

እልልታ ከሞት ላዳነኝ

እልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ

እልልታ ጠላቴን ለመታ

እልልታ ሕያው ላረገኝ

እልልታ ከሞት ላዳነኝ

ወጥመድ ተዘርግቶ በሞት ሸለቆ

ጠላት ሲጠብቅ ድብቅ ሽምቆ

አመለጥኩኝ ባንተ ነፍሴን ከሚሻ

ነፃ አወጣኸኝ ሆንከኝ መሸሻ

ምስጋና አምልኮ

ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ

አልጠገብኩም ዛሬም

እልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ

እልልታ ጠላቴን ለመታ

እልልታ ሕያው ላረገኝ

እልልታ ከሞት ላዳነኝ

ስለ ስሙ መራኝ በጽድቅ መንገድ

ነፍሴንም አዳናት ከአዳኞች ወጥመድ

አልተሰናከልኩም ባልፍም በሞት ጥላ

እግዚአብሔር አምላኬ ሆኖልኝ ከለላ

ወጥመድ ተዘርግቶ በሞት ሸለቆ

ጠላት ሲጠብቅ ድብቅ ሽምቆ

አመለጥኩኝ ባንተ ነፍሴን ከሚሻ

ነፃ አወጣኸኝ ሆንከኝ መሸሻ

ምስጋና አምልኮ

ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ

አልጠገብኩም ዛሬም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ