Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምርጫዬ ልክ ነው

Mirchaye Lik New

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አጣሁኝ ብዬ ከቶ አይቆጨኝም

ከዓለም የሆነውን ፈጽሞ አልመኝም

የቀረብኝ ሁሉ እንኳን ቀረ ያኔ

በጌታ በኢየሱስ ተውቧል ዘመኔ

ምን ቀረብኝ ምን ጎደለብኝ

የዚህን ዓለም ነገር ስለተውኩኝ

የቀረብኝ ሞት ነው የዘላለም ቁጣ

ወትሮስ ምን ሊኖረው ኢየሱስን ያጣ

አተረፈ እንጂ በነፍስም በሥጋው

ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነለት ዋጋው

ከንቱ ነው የምድር ንዋይ

የከበረውን አሻቅቦ ለሚያይ

ምርጫዬ ልክ ነው በእርግጥ ያዋጣል

ከዓለም ሀብት ክብር ኢየሱስ ይበልጣል

እውነቱ ለገባው ለበራለት ሐቁ

የተወደድክ ነህ የምትልቅ ከዕንቁ

የሙጥኝ ልበልህ እኔም በአንተ ልጽና

ከምንም የምትበልጥ በረከት ነህና

እንደሚርቅ እንዲሁ ሰማይ ከምድር

ኢየሱስን ማወቅ ነው ታላቅ ምስጢር

ብርሃን ከጨለማ አንድ እንዳልሆነ

ልዩ ነው አድራሻው በኢየሱስ ያመነ

ከንቱ ነው የምድር ንዋይ

የከበረውን አሻቅቦ ለሚያይ

ምርጫዬ ልክ ነው በእርግጥ ያዋጣል

ከዓለም ሀብት ክብር ኢየሱስ ይበልጣል

ሞት አለፈኝ

ውርደት አለፈኝ

ችግር አለፈኝ

ጌታ ስላለኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ