Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ታርደሃልና

Tardehalina

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ብርቱ መልአክ እንዲህ ሲል አወጀ

ማኅተሙን ለመፍታት ማነው የተዘጋጀ

በሰማይም በምድርም አልተገኘም ከቶ

መጽሐፉን ለመውሰድ ለመመልከት ከፍቶ

ግን አንተ ተገኘህ የታረድከው በግ

ለአንተ ተችሎሃል ይህንን ማድረግ

መጽሐፉን ወሰድከው ማኅተሙ ተፈታ

ሁሉን ድል ነሥተሃል ኢየሱስ ነህ ጌታ

ታርደሃልና ይገባሃል ክብር*4

ቀራንዮ ላይ እርቃንህን ተንጠልጥለህ

አሸንፈሃል በመስቀልህ ጥልን ገድለህ

በትንሳዔ ኃይል የሞትን ጣር አጥፍተህ

ድል ነሥተሃል ሰባቱንም ማኅተም ፈተህ

ከነገድ ከቋንቋ ሕዝብህን ዋጅተሃል

ካህንና መንግሥት ሕዝብን አድርገሃል

ክብር ይገባሃል*8

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ