እንደገና
Endegena
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የተዘጋ ምዕራፍ የተደመደመ
አሁን የማይባል ያኔ ላይ የቆመ
የፈረሰውን ቤት እንደገና ሠራ
ተስፋ ፈነጠቀ አዲስ ብርሃን በራ
ስንገዳገድ ሳለሁ በሕይወት ፈተና
ጉልበቴ ዝሎብኝ በዝቶብኝ ፈተና
ለነፍሴ ነግሬአት የመሞቴን ዜና
ጌታ አቁሞኛል ዳግም እንደገና
አዝማች · Chorus
እንደገና የወደቀችውን
እንደገና የዳዊትን ድንኳን
እንደገና አድሶ ቀይሯል
እንደገና የቀድሞ ታሪኳን
እንደገና በእኔም ሕይወት ጌታ
እንደገና ዘመናትን ቆጥሮ
እንደገና በክብር አቁሞኛል
እንደገና ታሪክን ቀይሮ
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሸለቆ ውስጥ ተበታትነው የወደቁ
ከሕያዋን ዓለም ፈፅመው የራቁ
ሠራዊት ሆነው ዳግም ተነሡ
ተአምርን ማድረግ ይችላል እርሱ
አዝማች · Chorus
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
የዘራሁትን ዘር በሐዘን በለቅሶ
በደስታ አሳጨደኝ ምርኮዬን መልሶ
የሐዘኔን ወራት ጌታ ተመልክቷል
ምላሴ በእልልታ አፌ ሳቅ ተሞልቷል
አዝማች · Chorus
እንደገና ምስኪኑን ከትቢያ
እንደገና አንሥተህ ከአፈር
እንደገና ሞገሱ ሆንክለት
እንደገና ክብርህን እንዲናገር
እንደገና ማዳንህን ላውራ
እንደገና ያ ሰው እኔ ነኝ
እንደገና ሰው አይሆንም ሲሉ
እንደገና ሰው ያደረከኝ
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ
እንደገና ክብር
እንደገና ሞገስ
እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው
ነገርን ሁሉ የሚለውጠው
እሱ የጠፋውን ያገኛል ፈልጎ
ዳግም ይሠራዋል አዲስ አድርጎ
አዲስ አርጎ አዲስ አርጎ
ይሰራዋል ውብ አድርጎ
ውብ አድርጎ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ