Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አትለፈኝ

Atilefegn

ትራክ 2 · 4:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ክብር ሞገሴ ግርማ ድምቀቴ ውበቴ

አለኝታዬ ጋሻ መከታ ዋስትናዬ

የሆነው ፊትህ የምናፈቀው ምወደው

ከሁሉ በላይ ህልውናህን ነው ምፈልገው

በፊትህ ስሆን ነዉ ደስታዬ

በፊትህ መዋረድ ነው ክብር እርካታዬ

በፊትህ ስሆን ነው አቅሜ

ነፍሴን ሳፈስ ነው ሚበዛው ሰላሜ

ዛሬም በፊትህ ደስ ብሎኝ እመጣለሁ

አባቴ ልልህ ጓጉቼ እመጣለሁ

ከእጅህ ሳይሆን አንተን ፈልጌ እመጣለሁ

የማለምደውን ክብር ናፍቄ መጣለሁ

ዛሬም በፊትህ ደስብሎኝ እመጣለሁ

አዲስነትህ አጓጉቶኝ እመጣለሁ

ከእጅህ ሳይሆን አንተን ፈልጌ እመጣለሁ

የማለምደውን ክብር ናፍቄ መጣለሁ

አተለፈኝ ሳትነካኝ

በመገኘትህ ሳትባርከኝ

ህልውናህን አትንፈገኝ

ጩኸቴ ፊትህ ሞገስካገኘ እባክህ ዳሰኝ

አተለፈኝ ሳትነካኝ

በመገኘትህ ሳትባርከኝ

ህልውናህን አትንፈገኝ

ጨለማው ብርሀን

በረሀው ለምለም እንዲሆንልኝ

አንዴ ከሰጠኸኝ ድፍረት

ለመቅረብ ወዳለህበት

ህልውናህን እሻዋለው

ክብርህን ስተገልጥ ላይ እወዳለው

ባለህበት

ፍፁም ህይወት

ፍፁም እርካታ ፍፁም ሙላት

ባለህበተ ፍፁም ደስታ

ይሞላኛል ሰላም እረፍት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ