ከመታወቅ
Kemetawek
ትራክ 9 · 5:43 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላካችን ይህ ነው የምንገዛለት
ፊቱ ደፋ ቀና ዘዉትር ምንልለት
እድሜ ዘመናችን የተሰጠንለት
እግዚአብሔር አምላካችን
ለመንግስቱ ሁሉ ሚገዛለት
አዝማች · Chorus
አምላካችን ድንቅ ነው
ከቃላትም በላይ ነው
አምላካችን ድንቅ ነው
ከመታወቅ ያለፈ ነዉ
ያለ ሚኖር ስሙ የሆነዉ
አልፋ ኦሜጋ እኔነኝ ያለው
በፅድቅ እውነት መንበሩን ያጸና
በክብር ሐይል በሞገስ በግርማ
ሊያይ ማንም በማይደፍረው ብርሃን
በክብር ያለ በዘላለም ዙፋን
ቁጥር 2 · Verse 2
ጥበብ እውቀት ማስፈራት ተጎናጽፏል
ሰማይን ያለ ምሶሶ ያቆመው
የምድር ስፋት ልኬት የወሰነው
ለባሕሩ ገደብ ያኖረለት
ለብርሀናት መንገድ ያበጀለት
ንፋስን ከመዛግብቱ ያወጣል
ደመናት ላይ ውሃን ይጭናል
ፍጥረት ሁሉ እሱን ይታዘዛል
ከመታወቅ ያልፋል የአንተ ማንነት
እጅህ ስራ የሰው ልጅ እንዴት ሊደርስበት
እጹብ ድንቅ እንጂ ሌላ ምን እንበልህ
ከአእምሮአችን በላይ እጅግ ከፍ ያልክ ነህ
አዝማች · Chorus
ለዘመንህ ጅማሬ የለህ
ለመገኘትህ ወሰን የለህ
ለእውቀትህ ገደብ የለህ
ለሓይልህ ወደር የለህ
ለዘመንህ ፍፃሜ የለህ
ለመገኘትህ ወሰን የለህ
ለእውቀትህ ገደብ የለህ
ለሓይልህ ወደር የለህ
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዴት ድንቅ ነህ
እንዴት ግሩም ነህ
አንተን የሚመስል
ማንም የለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ