Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጉልበቴ ሆይ

Gulbete Hoy

ትራክ 14 · 5:29 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የወደቀ ዳግም አይነሳም ወይ

የሳተስ ከፊቱ ደግሞ አይቆምም ወይ

አይኑ እንዳየ አይበይን ጆሮው እንደ ሰማ

የምስኪኑን ጩኸት አይቶ አያልፍ እሱማ

መስቀል ተሸክሞ መከተል ሲያቅተኝ

በጠባቡ መንገድ መጓዝ ሲሳነኝ

ነፍሴ እጅጉን ዝላ ተስፋዬ ተሟጦ

በትዕዛዛትህ ለመሄድ ውስጤ አቅም አጥቶ

የላሉ እግሮቼን ጉልበቴን አፀናህ

ዳግም እንደንስር ሃይሌን አደስክና

ጉልበቴ ሆይ ክበር ክበር

አቅሜ ሆይ ክበር ክበር

ዛሬም ረድተኸኛል እግዚአብሔር

ዛሬም አግዘኸኛል እግዚአብሔር

አቅሜ ሆንክልኝ እግዚአብሔር

ጉልበቴን አፀናህ እግዚአብሔር

ከበአል ነቢያት እንዳልተወራረደ

በኤልዛቤል ዛቻ ልቡ ወዲያው ራደ

ጥለኸው አላለፍክ ብርቱ ሰው ፍለጋ

የቀደመው ስራው ቅናቱ እንደሌለው ዋጋ

የፍቅር እንጎቻህን ዳግም ብላ አልከው

እረጅሙን ጉዞ በድል ወደህ ልታስጨርሰው

ለደካማው ሃይልን ይሰጣልና

ለወደቀ እጁን ዘርግቷልና

ዘወትር ሊረዳን እርሱ ታምኗልና

ይክበር ዘላለም ይብዛለት ምስጋና

ዛሬም ይረዳናል እግዚአብሔር

ዛሬም ያግዘናል እግዚአብሔር

አቅማችን ሆኗል እግዚአብሔር

ጉልበታችን ፀንቷል በእግዚአብሔር

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ