መዳኛ
Medagna
ትራክ 11 · 3:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የቅዱሳን ልብ ይታመንብሃል
በጎነቱ አንተ ነህ ይጠባበቅሃል
ጌታዬ ባንተ የተያዘ
አይጠፋም ባንተ ታገዘ
ይምጣ ይወራረድ አህዛብ አምላካቹ
የኔም ጌታ ይኸው ግርማው ይታያቹ
ልቆ ከፍ የሚለው ይውሰድ መስዋቱን
ይቀበል ምስጋና የአምላክነት ክብሩን
ሲል ለተወራረደ በስምህ ጀግኖ
ሃይልህ በዕርሱ ታየ ክብርህ በላዩ ዳምኖ
ባንተ የታመነውን በድል አሸለልከው
ክብርህን ስትገልጠው ስጋ ለባሸ አየው
አዝማች · Chorus
አምላክነትህ ይታይ በእኛም
ስለሆንከን ፅኑ መዳኛ
መዳኛ መዳኛ ነህ
ማምለጫ ማምለጫ ነህ
የአብርሃም የይስሀቅ የያዕቆብ አምላክ
ዛሬም በክርስቶስ የቅዱሳን አባት
ቁጥር 2 · Verse 2
ስምህ እቃ ጦራችን ይዘን እንወጣለን
ሞገስ ክብራችን ነህ እንታመንሃለን
አባትነትህ ታየ በኛ
ስለሆንከን ፅኑ መዳኛ
አዝማች · Chorus
መዳኛ መዳኛ ነህ
ማለፊያ ማረፊያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ