Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይምራል

Yimral

ትራክ 3 · 4:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነነዌ በሀጥያት ተዉጣ ተከባ

ሊያጠፋት ሲነሳ ህዝቡ ቢመለስ በብዙ ንስሀ

ቁጣውን አርቆ ምህረቱን አብዝቶ ህዝቡን ቢያስበው

ባርያው ማዘኑ ጌታን መሞገቱ እኮ ለምንነው

እግዚአብሄር ምህረቱ ሰፊ ነዉ

እግዚአብሄር ምህረቱ ጥልቅ ነዉ

ቅሉ ድንገት በቅሎ ከስሞ እጄ ቢያደርቀው

ክንድህ ላለፋበት ልብህ ከጨነቀው

እንዴትስ አይራራም አያዝነለት ልቤ

ግራና ቀኙን ለማያውቀው ህዝቤ

አለው እግዚአብሄር መሀሪ ነው

ይምራል ይታደጋል ይቅር ይላል

በእውነት ለሚመለስ ጌታ እኮ ይራራል

ያዝንለታል

ይምራል ይታደጋል ይቅር ይላል

በህዝቡ ድካም እሱ መች ይስቃል ይሳለቃል

አምላኩ ቢቀባው ጠላት ፊት አክብዶ

ህዝቡን የሚታደግ መስፍን ሊያደርገው ወዶ

ተጠልፎ ቢወድቅ በደሊላ ውጥን

አልነፈገው ሰጠው ዳግም ምህረቱን

በሞቱ እልፍ አስጣለው አስቦት ባሪያውን

በእውነት ለሚመለስ መሀሪ ነው

መንፈሱን ለሰበረ አዛኝ ነው

በቃሉ ለሚርድ ለትሁት ሰው

እጅግ ያበዛታል ምህረቱን

ይምራል ይታደጋል ይቅር ይላል

የእንደገና አምላክ እግዚአብሔር ይራራል ይቅር ይላል

ይምራል ይታደጋል ይቅር ይላል

በህዝቡ ድካም እሱ መች ይስቃል ይሳለቃል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ