Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አደራ ነው

Adera New

ትራክ 10 · 4:44 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በስልጣንህ ቃል ዓለምን በያዝከው

የህይወቴን ዳርቻ ዘመን በወሰንከው

ባንተ ህያው ሆኜ ወጣለው ገባለው

እንኳን በእጄ የያዝኩት እስትንፋሴም ያንተው ነው

ማስተዋልን ስጠኝ

ኢየሱስ ሆይ አስበኝ

ማስተዋልን ስጠኝ

ጌታዬ አስበኝ

ያለው ተከማችቶ ሲሞላ ጎተራው

መሰለው ዘመኑን መንዝሮ ሚበላው

ተላላ አላዋቂ ሆኖ አለፈች ነፍሱ

ሲሻ ዘላለሙን ታምኖ ሊኖር ራሱን

ታምኖ ሊኖር ኪሱን

ጉልበቱን ባልሳመ ክንዱን ባልተመካ

ብርታት የሰጠውን አምላኩን ቢረዳ

እድሜው እንደ እንፋሎት ነው ለካ

እርዳኝ እኔን አዎ

አግዘኝ እኔን አዎ

እንድታመንልህ አዎ

ደስ እንዳሰኝህአዎ

የላቡን ዋጋ ፍሬ ሚጠብቅ

የለፋ ሰው ነው ደሞዝ የሚጠይቅ

እንዲሁ በነፃ ፀጋን ስትሰጠኝ

ባልደከምኩበት ተመን ካወጣሁኝ

ያን ጊዜ ውድቀት ከጀለኝ

አደራህን ከእጄ ምትቀበልበት

ቀን አለ በፊትህ የምጠየቅበት

ነህና የሁሉ ባለቤት

እርዳኝ እኔን አዎ

አግዘኝ እኔን አዎ

እንድታመንልህ አዎ

ደስ እንዳሰኝህአዎ

እንዲሁ መጣሁ እንዲሁ ሄዳለው

ሁሉን የሰጠኝ በአደራ ነው

ትምክህቴ ታዲያ በምን ነው

ሁሉ እኮ የእግዚአብሄር ነው

አክብሬ ስኖር አደራዬን

እቀበላለው ሽልማቴን

ናፍቆት የልቤ ጥማት

ታማኝ ባሪያ ሲለኝ መስማት

የሁሉ አደራ ነዉ አዎ

የተቀበልኩት አዎ

አንድ ቀን ፊቱ አዎ

ምጠየቅበት አዎ

(ማስተዋልን ስጠኝ ኢየሱስ ሆይ አስበኝ

ማስተዋልን ስጠኝ ጌታዬ አስበኝ)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ