እናመልክሀለን
Enamelkihalen
ትራክ 5 · 5:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዴት ሰው አንተን ከማምለክ ኃላ ይቀራል
ምክኒያት የለኝም ቢል እንኳን ፍጥረት ይበቃል
የእጅህን ስራ እያየን እናደንቅሀለን
አዝማች · Chorus
እኔና ቤቴ ግን እግዚያብሄር ሆይ እናመልክሀለን
በዝማሬ እናመልክሀለን
በእልልታ እናመልክሀለን
ዝቅ እያልን እናመልክሀለን
በደስታ እናመልክሀለን
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉን ስትሰራ አጋዥ አላሻህም ረዳት አልጠራህም
ብቻህን ፈጠርክ በሀይል በችሎትህ
ለቃልህ ታዞልህ
ቀላያት ፈጠርክ በአፍህ ቃል
ምድርን አፀናህ በአፍህ ቃል
ጨረቃን ለሊት ሾመሀታል
ቀኑን ስትጠራ ፀሀይ ወጥቷል
ኦ ጥበብህ ኦ ስራህ
ኦ ችሮታህ ኦ እውቀትህ
ባለጠግነትህ ጥልቅ ነው
ጥበብ እውቀትህ ጥልቅ ነው
ሰማይ ምድሩ ያንተ ነው
ሀይልም ስልጣንም በእጅህ ነው
እንዳንተ ያለ ማንም እንደሌለ ሰምቼ ነበረ
አየችህ አይኔ ልዑል ካንተ ሌላ እንደሌለ የከበረ
አዝማች · Chorus
ገናናነትህን አወራለሁ
አምላክነትህን አወራለሁ
ሀይልህን ብርታትህን አወራለሁ
ኤልሻዳይ መሆንህን አይቻለዉ
ኦ ጥበብህ ኦ ስራህ
ኦ ችሮታህ ኦ እውቀትህ
ባለጠግነትህ ጥልቅ ነው
ጥበብ እውቀትህ ጥልቅ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰማይ ምድሩ ያንተ ነው
ሀይልም ስልጣንም በእጅህ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ