እለምንሃለሁ
Eleminihalehu
ትራክ 1 · 5:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተማ ፍቅር ነህ የማትለዋወጥ
መውደድህ ፍፁም ነው ብርቱ ማይናወጥ
የመስቀሉ ስራ ምስክር ነው
የፍቅር ልክህን ጥጉን ያሳየው
ቀረጽከኝ በመዳፍ ላትጥለኝ ዘላለም
ባንተ በኩል እኔ ስጋት የለኝም
እኔ ምፈራው እኔን ነው
የምህረትህ ጥላህን እንዳለምደው
የቆምኩ መስሎኝ እንዳልወድቅ
ከሕያው ምንጩ ጋር ካለቱ ልጣበቅ
አረ እኔ ማላምነው እኔን ነው
የያዘኝ እጅህን እንዳልገፋው
የቆምኩ መስሎኝ እነዳልወድቅ
ከሕያው ምንጩ ጋር ካለቱ ልጣበቅ
አዝማች · Chorus
የምወደው ልጄ እሱ ነው ባልከው
በኢየሱስ እለምንሃለሁ
እራሱን ባዶ አርጎ ከላይ በመጣዉ
በኢየሱስ እለምንሃለሁ
ሁሉ በሁሉ ሆኖ ዝቅ ዝቅ ባለው
በኢየሱስ እለምንሃለሁ
የፈቃድህን ጽዋ ጭልጥ ባደረገው
በኢየሱስ እለምንሃለሁ
በፊትህ ሊያቀርበኝ እንደ ደም ላብ ባላበው
ስለ ኢየሱስ እለምንሃለሁ
ታዞ በመስቀል ላይ ነፍሱን በሰጠው
ስለኢየሱስ እማፀንሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ልመናዬም ፀሎቴ ይህ ነዉ
በቤትህ ሁሌ እንድኖር ነው
እባክህ ብዬ ምጠይቅህ
ፍጻሜ እንዲያምር በፊትህ
እባክህ ብዬ ምለምንህ
ህይወቴ እንዲያምር በቤትህ
ዕድሜዬን በሃዘን ከመያስጨርሰኝ
ከክፉ ውሳኔ እባክህ ጠብቀኝ
ሕይወቴን አጉብጦ ከሚያወርድ መቃብር
ከጠማማ እርምጃ ሰውረኝ እግዚአብሔር
እንዳልገኝ በክፎች ማህበር
አይመረኝ የሐጢያተኞች ወንበር
ፍጻሜው ሞት ከሆነ ተድላ
አድነኝ እባክህ ነፍሴ ሳትበላ
እባክህ ብዬ ምጠይቅህ
ፍጻሜዬ እንዲያምር በፊትህ
እባክህ ብዬ ምለምንህ
ሕይወቴ እንዲያምር በቤትህ
ቁጥር 3 · Verse 3
በሚሞት ስጋዬ ሃጥያት እንዳይነግስ
በጥርሴ ነክሼው ልመስልህ ልገስግስ
በመንገድ ሊያስቀረኝ ልሚታገለኝ ስጋ
ስለምን ምኞቱን ለመፈጸም ልትጋ
ፊትህን አትሰውርብኝ ለፍቃዴ አትተወኝ
ለማይረባ አዕምሮ አሳልፈህ አትስጠኝ
ይልቁንም መንፈስህን ሙላኝ
እሱ ነው ከግብ የሚያደርሰኝ
በኃለኛው ዘመን ፊትህ እንዳላፍር
ዘይቴ አይለቅ ከመቅረዜ ስር
እባክህ ብዬ የምለምንህ
እንዳትሰውረው ከኔ ፊትህን
አዝማች · Chorus
አስገዛልኝ ነፍሴን ማርከህ
ተለመነኝ ስለልጅህ
ተለመነኝ ስለ ልጅህ
ተለመነኝ ስለ ልጅህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ