ዉዴ
Wude
ትራክ 12 · 5:58 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለኔ ሀጥያት የሞተልኝ
ነፍሱን አሳልፎ የሰጠኝ
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር
ከቶ ለማንም የለም
ነፍሱን በፈቃዱ የሰጠ ለአዳም ዘር
ወደ ምድር መጣ ቤዛ ሊሆን ለአለም
ዘወትር በአብ ፊት ስለ እኛ ሚማልደው
የአዲስ ኪዳን ዋስ እየሱስ ፍቅሩ ማያረጀው
አዝማች · Chorus
ኦ ውዴ አንተ የኔ እኔም ያንተ
ላንለያይ ኪዳን ገብተን
መሀላ አለ መሀላችን
ዘላለማዊ ነው ፍቅራችን
ቁጥር 2 · Verse 2
የወደደን መውደድ ምንኛ ቀላል ነው
በዳይ በእጁ ይዞ መማር ግን ፈታኝ ነው
በፍቅሩ አሰረኝ ይህ ሆኖ በህይወቴ
ጠላቱ ሆኜ ሳለው እየሱስ ገብቶ ቤቴ
አዝማች · Chorus
ኦ ውዴ አንተ የኔ እኔም ያንተ
ላንለያይ ኪዳን ገብተን
መሀላ አለ መሀላችን
ዘላለማዊ ነው ፍቅራችን
ቁጥር 3 · Verse 3
ደካማ ሰው ሳለሁ ቀንበር የተጫነኝ
ወደ እኔ ነይ ብሎ ከሸክሜ አሳረፈኝ
ልቡ የዋህ ትሁት ቀንበሩም ቀሊል ነው
ፍቅሩ ጠሊቅ ውሀ ማለቂያ የሌለው
ይቅርብኝ ይቅር ያላንተ መኖር
ይቅርብኝ ይቅር ያላንተ መኖር
ይቅርብኝ ይቅር አንተ የሌለህበት
መንገዴም አይቀና ያገኘኛል ሞት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ