እጠጋሀለው
Etegahalew
ትራክ 4 · 6:13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነብሴ በዛለች ጊዜ እግዚያብሄር ሆይ አሰብኩህ
እግዚያብሄር ሆይ አሰብኩህ
ክፉ ቀኖች ከፊቴ በመጡብኝ ሰአት
አዳኜ ሆይ አሰብኩህ
እግዚያብሄር ሆይ አሰብኩህ
የጠላቶቼ ሀይል እጅጉን በርትቶ
ሊውጠኝ ሚፈልግ ሲዞረኝ አብዝቶ
በጨነቀኝ ጊዜ ስምህን ጠራሁት
ከመቅደስህ ቃሌን ሰማህ የኔን ጩኸት
በበዛው ድካሜ ገለጥክ ብርታትህን
ከወደረኛዬ ይልቅ አብዝተህ አቅሜን
ስለዚህ ሁልጊዜ እጠጋሀለው
ትድግናህ ደህንነትም ካንተ ዘንድ ነው
በምትገኝበት እፈልግሀለው
ስለዚህ አብዝቼ እጠጋሀለው
አዝማች · Chorus
ደግሞ ስጠጋህ ሀዘኔ በደስታ
ደግሞ ስጠጋህ መቅበዝበዝን በእርጋታ
ደግሞ ስጠጋህ እምነትን በስጋት ፋንታ
ቀይረኸዋል ክበርልኝ የኔጌታ
ካደከመኝ ይልቅ የምታበረታኝ
ካስፈራራኝ ይልቅ የምታስመካኝ
ካጨለመብኝ ይልቅ የምታነጋው
እንድትልቅ አውቃለው መደገፌም ባንተ ነው
እጅህ እጄን ስለያዘው አርፌአለው
እኔም የአቅሜን ሙጥኝ እልሀለው
የዘላለም ክንድህ ከበታቼ ነው
ምህረትህ ቸርነትህ ዋስትናዬ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ደግሞ ስጠጋ ፍርሀቴን አጀግነሀል
ደግሞ ስጠጋህ ልቤን በቃልህ ደግፈሀል
ደግሞ ስጠጋህ እጆቼን ሰልፍ አስተማርክ
አሸናፊ አረከኝ የጠላቴን ጀርባ ሰጠህ
እግዚያብሄር አለቴ
አምባዬ ነህ መድሀኒቴ
ደግ ልብህ ያስጠጋል
መልካም ክንድህ ያስመካል
አዝማች · Chorus
እጠጋሀለው(3) ሰላሜ ባንተ ነው
እጠጋሀለው(3) እረፍቴ ባንተ ነው
እቀርብሀለው (4)ሰላሜ ባንተ ነው
እቀርብሀለው (4) ደስታዬ ባንተ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ