እወድሃለሁ
Ewedihalew
ትራክ 7 · 5:28 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ካወኩህ ጀምሮ ከተጠጋሁህ
በጥላህ ስር ሳድር አንተን ካመንኩህ
የማውቀው ይኼን ነው ስላንተማንነት
ተረትም አይደለም በአይኔ ያየሁት እውነት
አይሰለችህም ስትወደኝ
አይሰለችህም ስትምረኝ
አይሰለችህም ለኔ መራራት
አልታከተህም እኔን ለመርዳት
አይሰለችህም ከኔ ጋር መሆን
አይሰለችህም ማድመጥ ውስጠቴን
አይሰለችህም ስትመራኝ
አልታከተህም ስትሸከመኝ
አዝማች · Chorus
ምን እልሃለሁ ቃሌ ደካማ ነው
አዉጥቼ አውርጄ ምለው አጣው
ብቻ እወድሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
እውነትህ ሲፈርድ ሐጢያት በደሌን ገልጦ
ምህረትህ ከደነው እኔን መውደድህ በልጦ
ፍቅር ምክኒያት ሆኖ ፊትህ አቀረበኝ
አንተ ጋር የሚያስጠጋኝ ሌላማ ምን ብቃት ነበረኝ
የፀጋህ ጉልበት ወዳንተ አቀረበኝ
አንተ ጋር ሚያስጠጋኝ ሌላማ ምን ድፍረት ነበረኝ
ምን እልሃለሁ ቃሌ ደካማ ነው
አዉጥቼ አውርጄ ምለው አጣው
ብቻ እወድሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ እወድሃለሁ እኔ እወድሃለሁ
ውስጤ ያለው ብዙ ነዉ
ቃሌ ግን ትንሽ ነዉ
እራርተህልኝ እየታገስከኝ
ይቅር እያልከኝ ብዙ ምረኸኝ
ዛሬ አደረስከኝ
እየመከርከኝ እየገሰፅከኝ
በክንፍህ ሸፍነህ እጄን ይዘኸኝ
ዛሬ አደረስከኝ
አዝማች · Chorus
ምን እልሃለሁ ቃሌ ደካማ ነው
አዉጥቼ አውርጄ ምለው አጣው
ብቻ እወድሃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ እወድሃለሁ እኔ እወድሃለሁ
ውስጤ ያለው ብዙ ነዉ
ቃሌ ግን ዉስን ነዉ
ትላንቴ ያለፈው በበጎነትህ
አምና ካቻምናዬም ቢያወሩ ምህረት ቸርነትን
አሁንም ምኖረው አንተን ተማምኜ
ማይንሸራተተው ፍቅርህነው ዋስትና ማህተሜ
ቁጥር 5 · Verse 5
አትለወጥም ለዘለዓለም
አትቀየርም ስለዚህ ነገን አልፈራም
አንተ እኮ አትለዋወጥም
ነገን አልፈራ እኔም
አንተ እንደው አትቀያየርም
ነገን አልፈራ እኔም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ