በቃልህ
Bekalih
ትራክ 8 · 5:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዛሬም እግሮችህ ስር ቁጭ እላለሁ
የነፍሴ ርሃቧም ይሄው ነው
ቃል ይውጣ ተናገር ካፍህ
እኔም እሰማለው ድምፅህን
በቃልህ ተናገረኛ
እኔም ሰማሀለው ዝም አትበለኛ
በለኛ ተናገረኛ
እኔም ሰማሀለው ዝም አትበለኛ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው ከእግዚያብሔር አፍ በሚወጣ ቃል
እንጂ በእህል ውሃ ብቻ መች ይኖራል
ተስፋ አተው የደረቁ አጥንቶች ቆመዋል
ካፉ ቃል ሲወጣ ለምልመው ታይተዋል
የህይወት ምንጭ ነው ቃልህ
ልብ ያቀናል ደግሞም ምክርህ
ማይለወጥ ሚለዉጥ ቃልህ
ይምጣ ይፍሰስ በማደሪያህ
አዝማች · Chorus
ቃልህ ፍፁም እውነት ቃልህ ፍፁም ህይወት
ወጥቷል እና ከአንተ አንደበት
ምን ስህተት ሊገኝበት
ቃልህ ፍፁም እውነት ቃልህ ፍፁም ህይወት
ወጥቷል እና ከአንተ አንደበት
ምን ግድፈት ሊገኝበት ምን ግድፈት ሊገኝበት
ወጥቷል እና ካንተ አንደበት
ምን ስህተት ሊገኝበት
ወጥቷል እና ካንተ አንደበት
አዝማች · Chorus
በቃልህ ተናገረኛ
እኔም እሰማሀለው ዝምአትበለኛ
በለኛ ተናገረኛ
እኔም ሰማሀለው ዝም አትበለኛ
ቁጥር 3 · Verse 3
ምድረበዳ አናውጦ ዝግባን የሚቆርጥ
የሌለን እንዳለ ጠርቶ የሚለውጥ
ቅዱሳኑን ልብ በሃይል የሚያስታጥቅ
አረ እኔ ናፈቀኝ በድምፅህ መጥለቅለቅ
አዝማች · Chorus
በለኛ ተናገረኛ እጠብቅሃለው ዝም አትበለኛ
በለኛ ተናገረኛ እታዘዝሃለው ዝም አትበለኛ
እታዘዝሃለው ዝም አትበለኛ
እታዘዝሃለው ዝም አትበለኛ
እጠብቅሃለው ዝም አትበለኛ
በህይወት እኖራለው ዝም አትበለኛ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ