እንዳንተ መሀሪ
Endante Mehari
ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከእልፍኟ ማልዳ ፀሀይ ስትወጣ
ታበስር የለ ወይ ሌላ ቀን እንደመጣ
የእግዚያብሔር ምህረት የተገለጠባት
ለሀጥዕ ለፃድቁ አድሎ በሌለበት
ትእግስቱን ትሰብካለች የርህራሄውን ስፋት
ትላለች ይኼው ሌላ ቀን እግዚአብሔር ያወጣት
በቅድስናህ ፊት ማን መቆም ይችላል
እንኳን ስጋ ለባሽ ተራራውም ጤሷል
ነውር በሌለበት በአዲስ ኪዳኑ በግ
ወደ ፀጋው ዙፋን ተቻለ በእምነት መቅረብ
አዝማች · Chorus
ኦሆ እንዳንተ መሀሪ የለም*2
ኦሆ እንዳንተ ይቅር ባይ የለም*2
ቁጥር 2 · Verse 2
የሀጥያታችን ብዛት ቁጣህን ቢያነደው
ምትክ ሆኖ እየሱስ በላዩ አበረደው
ፃድቅ ሆኖ ሳለ ሃጥያት የማያውቀው
የሁላችንን በደል በሱላይ አኖርከው
እዳችንን ሊከፍል ደቀቀ ቆሰለ
መድሀኒአለም በመስቀል ላይ ዋለ
አዝማች · Chorus
ምህረቱ ብዙ ነው ለዘላለም ነው
ይቅርታው ብዙ ነው ለዘላለም ነው
ርህራሄው አያልቅም ለዘላለም ነው
ማለዳ አዲስ ነው ለዘላለም ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ