አመሰግናለሁ
Ameseginalew
ትራክ 6 · 6:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማልዶ ስነሳ ምከውነውን
ውጥኔን ዘዉትር ፊትህ ላኑረው
ፈቃድህ በጎ ፍፁም ደስ እንዲያሰኝ
የህይወቴ መርህ ሰንደቅ ይሁነኝ
ምኞቴን ይዘህ ስትከለክለኝ
ጓዳዬ በእልልታ በአምልኮ ይድመቅልኝ
የመዳንን ቀንድ ኢየሱስን ሰጥተኸኝ
ቀረብኝ ምለው እኔኑ አሳፈረኝ
አዝማች · Chorus
አመሰግንሃለሁ ስላልሆነው ስላልተሳካው
አመሰግንሃለሁ ሀሳብህ ሁሌ መልካም ነዉ
አመሰግንሃለሁ ያለኝ ሁሉ ማይገባኝ ነው
አመሰግንሃለሁ ያረክልኝ ብዙ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እልፍ ነው ያረክልኝ ችዬም አልቆጥረው
ጥቂቱን ብትነሳኝ ልቤ እሱን ናፈቀው
በእንባዬ የሞገትኩህ ሳይሆን የቀረው
አልፎ ዞሬ ሳየው ለካ ለመልካም ነዉ
ቁጥር 3 · Verse 3
ካልሆነልኝ ያልኩት ቀርቶብኝ ጠቀመኝ
መልካም አይተህልኝ ከልክለህ አዳንከኝ
ማግኘት ብቻም አይደል ማጣትም በጎ ነው
ምኞቴ ሞልቶልኝ ቢያጠፋኝ ምን ድል ነው
አዝማች · Chorus
አመሰግንሃለሁ ስላልሆነው ስላልተሳካው
አመሰግንሃለሁ ሀሳብህ ሁሌ መልካም ነዉ
አመሰግንሃለሁ ያለኝ ሁሉ ማይገባኝ ነው
አመሰግንሃለሁ ያረክልኝ ብዙ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ፀሎቴን ስትመልስ ወዳጅ ሰበሰብኩኝ
ዝም ያልከኝ ሲመስለኝ በእንባዬ ታጠብኩኝ
ተድላን ስታጠግበኝ ከእኔ ጋር ነህ አንዳላልኩ
ያሰብኩት ሳይሞላ የተውከኝ መሰለኝ
ድምፅህ ሲርቅብኝ እስኪመስል የሌለህ
በፀጥታ ውስጥም በዝምታም አለህ
ብትሰጥ ብትነሳ ፃድቅ ነህ ትክክል
ልስማማ ከሃሳብህ ፈቃድህን ልተል
ከሃሳብህ ጋር እስማማለሁ
አንተ ያልከውን ተቀብያለሁ
ባይገባኝም የማልፍበት
ግን አውቃለሁ የአንተን መልካምነት
ግን አውቃለሁ የአንተን በጎነት
ግን አውቃለሁ የአንተን ፃድቅነት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ