ታሪኬ
Tarike
4:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔ ምን ሕይወት አለኝ? ከሰጠኸኝ ሌላ?አሃ
እኔ ምን ታሪክ አለኝ? ከሆንህልኝ ሌላ?
እኔ ምን ትምክህት አለኝ? ከመስቀልህ ሌላ! አሃ
ካንተ ውጭ ምን ተስፋ አለኝ? ከእንግዲህ በኋላ!
ቁጥር 2 · Verse 2
ታሪኬን ለመንገር ብጀምር፣
ምን አለ ምሕረትህ ከጻፈው በቀር የሚነገር፣
ቀለም አልባ ሕይወቴን ይቅርታህ አቅልሞ፣
ሰማያዊ አ’ረገው በደም አትሞ፣
ጣዕም አልባ ሕይወቴን ፍቅርህ ቀምሞ፣
ጣፋጭ አደረገው የሚተርፍ ደሞ
አዝማች · Chorus
ያለሁት በምሕረትህ፣ የሚያኖረኝ ችሮታህ፣
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሄ ነው ታሪኬ ይመሰገን ስምህ፤
ሽረኸው ባርነቴን፣ ዐወጅኸው ነጻነቴን፣
ይሄ ነው ታሪኬ ይመሰገን ስምህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ስርዝ ድልዝ ነበር የተሞነጫጨረው፣
ጨለማዬን ገፍፈህ በብርሃን እስክትጽፈው፣ ስታትመው ስሜን በዘላለም መዝገብ፣
ያን ጊዜ ታሪኬ ጀመረ መነበብ
አዝማች · Chorus
ያለሁት በምሕረትህ፣ የሚያኖረኝ ችሮታህ፣
ቁጥር 5 · Verse 5
ይሄ ነው ታሪኬ ይመስገን ስምህ፤
አስዋብከው አድራሻዬን፣ ቀይረህ ፍለጋዬን፣
ይሄ ነው ታሪኬ ይመስገን ስምህ
ቁጥር 6 · Verse 6
ከእንግዲህ ምኖረው የእኔ ሕይወት፣
በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት፣
ለወደደኝ ራሱን ለሰጠኝ፣
ለዓለም ሞቼ ለእ’ሱ ሕያው ነኝ
ኢየሱስ (*6) የኔ ታሪክ የኔ ሕይወት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ