Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጠንነት ነው ወይ

Teninet New Wey

6:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ብዙ ብወድህ፣ ብዙ ምረኸኝ፣

አብዝቼ ብጠጋህ፣ ብዙ ትተህልኝ፣

የኔማ ፍቅር ሁሉ በምክንያት፣

ያንተ መውደድ ግን ያለ ስሌት

ፍቅርህ ሲለካ ሲመዘን፣

ነፍስ እስከ መስጠት ሚመዝን፥

ፍቅርህ ሲመዘን ሲለካ፣

እስከ መስቀል ሞት ነው ለካ

እወድሃለሁ አምላኬ

እወድሃለሁ የኔ ሕይወት

አንተን መውደድ ልቤ ውስጥ ያለው

የአክብሮት ፍርሀት የሞላው

የፍቅርህን ጥልቀቱን እያሰብኩኝ

አንተን መውደድ አክብሮት ተሞላሁኝ

ወደር የሌለው መልካምነትን፣

‘ማይመረመር ጠሊቅ ፍቅርህን፣

ይህሁሉ አይቼ ባልወድህ አይገርምም ወይ?

የማይለወጥ የማይናወጥ፣

‘ማይንሸራተት ‘ማያውቀውን ወረት

ፍቅርህን አይቼ ባልወድህ አይገርምም ወይ?

አይገርምም ወይ ባልወድህ? (*2)

ጤንነት ነው ወይ ባላመልክህ? (*2)

አንድ ቀን ቢያበቃስ ብዬ ‘ማልሠጋበት፣

ግለቱ የማይበርድ ዘመናት ቢያልፉበት፣

ከምረግጣት ምድር በላይ ‘ምታመነው፣

ጌታ ባንተ ፍቅር በማይለወጠው

በኔ ሁኔታ ያልተጀመረ፣

በኔ አመል ጠባይ ያልተቀመረ፣

መነሻው ራስህ ከማንነትህ፣

ከፍቅር ልብህ ከመልካም ባሕርይህ

ስበረታ አይጨምርም፤

ስደክም አይቀንስም፤

ፍቅርህ ያው ነው ዘላለም (*2)

እወድሃለሁ አምላኬ

እወድሃለሁ የኔ ሕይወት

አንተን መውደድ ልቤ ውስጥ ያለው

የአክብሮት ፍርሀት የሞላው

የፍቅርህን ጥልቀቱን እያሰብኩኝ

አንተን መውደድ አክብሮት ተሞላሁኝ

ወደር የሌለው መልካምነትን፣

‘ማይመረመር ጠሊቅ ፍቅርህን፣

ይህሁሉ አይቼ ባልወድህ አይገርምም ወይ?

የማይለወጥ የማይናወጥ፣

‘ማይንሸራተት ‘ማያውቀውን ወረት

ፍቅርህን አይቼ ባልወድህ አይገርምም ወይ?

አይገርምም ወይ ባልወድህ? (*2)

ጤንነት ነው ወይ ባላመልክህ? (*2)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ